መጽሃፍ – ስለ ወያኔ አወዳደቅ!

የወያኔ መሪዎች እጃቸው ከመያዙ በፊት የቀራቸውን አማራጮች ሁሉ እንደሚጠቀሙ ግልጽ ነው።
ለአብነት በመቐለ ወይም በአካባቢው ባሉ ገጠሮች ተበታትነው ሊሸሸጉ ይችላሉ። በኢትዮጵያ ወታደሮች አሰሳ በቀላሉ የማይገኙ የምድር ውስጥ ዋሻዎችን ቀደም ብለው ገንብተውም ሊሆን ይችላል። በመካከሉ በገንዘብ ሃይል ወደ ውጭ አገር የማምለጥ እድል ለማግኘት መጣራቸው የማይቀር ነው። ዳግም ተመልሰው ተጽእኖ ፈጣሪ መሆን ግን አይችሉም። ያለቀለት ጉዳይ ነው።
የቀረ ነገር ቢኖር ስለ ወያኔ አወዳደቅ (ከመነሻው እስከ መድረሻው) አንድ ተነባቢ መጽሃፍ ማሳተም ነው። ይህን የፍጻሜ ጦርነት ታሪክ ለመጻፍ ፍላጎት ቢኖረኝም ስራው ቀላል እንደማይሆን ከወዲሁ ይታየኛል። በእውነቱ የኢትዮጵያ ደራስያን ቀድመውኝ ሚዛኑን የጠበቀ መጽሃፍ ይጽፉ ዘንድ እመኛለሁ።
close

Leave a Reply