ቀይ ዘመን – የኤሊ ጉዞ!

ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት 21 ወራት የደከምኩበት በአይነቱ ልዩ የሆነው አዲሱ መጽሃፌ በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ፣ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ለንባብ ለመብቃት እንደ ኤሊ እየተጉዋዘ ይገኛል።

የዚህ መጽሃፍ ትረካ ታሪኮች ከ1900 እስከ 1999 ያለውን ጊዜ የሚሸፍኑ ቢሆንም፥ በድህረ ታሪኩ እስከ 2021 ላለው ክስተት በቂ ሽፋን ይሰጣል። “ከግራኝ አሕመድ እስከ አብይ አሕመድ” የሚል ቅጥያ አርእስት ለመያዝ ግን በ’ውነቱ ብቁ አይደለም።

(በዚህ አጋጣሚ በአካባቢያችን የፖለቲካ አካሄዱ “የኤሊ ጉዞ” የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው መሪ ማን ነበር?)

ዞረም ቀረ 400 +/- ገጾች የያዘው አዲሱ መጽሃፌ “ቀይ ዘመን” እንደሚባል መግለጼ ይታወሳል። ቅጥያ አርእስቱ – “ኢትዮ ኤርትራ 101” የሚል ነው።

ለዚህ መጽሃፍ የተለያዩ የሽፋን ዲዛይን መነሻ አሳብ እየደረሰኝ ነው። በውነቱ ገና አልረካሁም። የተሻለ አሳብ ያላችሁ ባለሙያዎች ttgebreab@gmail.com ላይ ትልኩልኝ ዘንድ እጠብቃለሁ። ለአሸናፊው አሳብ ገጽ ሁለት ላይ ምስጋና ወይም እውቅና እሰጣለሁ!

close

3 thoughts on “ቀይ ዘመን – የኤሊ ጉዞ!”

  1. ዘርኢት ዕጉስ

    ዋላኳ ብዙሕ መጻሕፍቲ ዘየንበብኩ እንተኾንኩ በተን ክሳብ ሕጂ ዘንበብክወን መጻሕፍትን ናይ ኣጸሓሕፋኻ ክእለት ኩሉ ግዜ ካብ ዘድንቑኻን ዝሕበኑልካን ኤርትራዊ እየ። ክሳብ ሕጂ ብጣዕሚ ዕጉብን ፈረቓንየ ። ታሪኽና ኣብ ምስናድ ትገብሮ ዘለኻ ዓቢ ኣስተዋጽኦ ቀጽሎ ጥራይ እየ ዝብለካ።

    1. ከማኻ ዝኣመሰሉ ደረስቲ 10 ኣብ ቀርኒ ኣፍሪቃ ተዝፈርዩ ክንደይ ጽቡቅ ነይሩ። ብፍላይ ነቶም ታሪኾምን ዶባቶምን ዘይፈልጡ ብሃጽያዉያን ዝደንቆሩ ሕብረተሰብ። እንኳዕ ኤርትራዊ ኮንካ። ብዝተወለድካሉ ከይትጠፍእ ዘምሃሩዃን ታሪኽካ ኣፍሊጦም ታሪኽ ሃገርካን ክትምህር ዝገበሩካ ኩቡራት ስድራቤትካን ክምስገኑ ዪግባእ። ቀይ መሰመር ግነ ክሳብ 2021 ክትጽሕፋ ኣለካ መበልኩ። ምክንያቱ ቀይ መሰመር ዝብተኸሉ ዓመት ኮይኑ ይስመዓኒ። ቀጽሎ ታሪኽ ሰውራን ብሰፊሕ ተተዳልዉ ጽቡቕ ነይሩ። ካብ ኣደናቂካ ፍረሂወት ኤርትራዊ እየ።

Leave a Reply