ባዶ ትእቢት!

ከሶስት ቀናት በፊት ደራሲና ፖለቲከኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር ያደረገውን ቆይታ ተከታተልኩ። ቃል በቃል ባይሆንም እንዲህ አለ፣
– የወያኔ መሪዎች ራሳቸውን እዚህ ችግር ውስጥ ለምን ከተቱ? ስልጣኑ ቢቀርባቸውም ኢኮኖሚው በእጃቸው ነበር። ኢኮኖሚውን የተቆጣጠረ ደግሞ ፖለቲካውን በእጅ አዙር ማዘዝ ይችላል። የወያኔ መሪዎች እንዴት ይህን ማሰብ ሳይችሉ ቀሩ? አምላክ ሊቀጣቸው ፈልጎ ይሆን? –
በርግጥ የአንዳርጋቸው መገረም ወይም ጥያቄ የኔም ጭምር ነው። ወያኔ በተሳሳተ ስሌት ፈንጂ ረገጠች። የተሸወደችበት መነሻ “ባዶ ትእቢት” ይመስለኛል።
close

Leave a Reply