ባጫ ደበሌ – ገባ መቀሌ!!

መቸም ዘመን ይለወጣል። “የጊዜ እንጂ የሰው ጀግና የለውም” የሚለው አባባል ለጄኔራል ባጫ ደበሌ በትክክል ይሰራል።
“ከኛ በላይ ማን ጀግና” እያሉ ለእሩብ ዘመን ጉራቸውን የቸረቸሩ ወያኔዎችን ባጫ ደበሌ እያሳደደ ሃገረ ሰላም ጎሬ ሲጨምራቸው ማየት በጣም ያዝናናል። ጄኔራል ባጫ ደበሌ ይህን ታሪካዊ ጦርነት ከመሩ ጄኔራል መኮንኖች አንዱ ለመሆን በመብቃቱ በ’ውነቱ በጣም እድለኛ ነው። እንደ አወዳይ ጫት ሲቅሙት የኖሩ የቀድሞ አለቆቹን እሱ በተራው እንደ በለጨ ቃማቸው።
ጄኔራል ባጫ ደበሌ እንደጀመረው የወያኔ መሪዎችን ከሃገረሰላም ዋሻ ጎትቶ በማውጣት ለፍርድ እንደሚያቀርባቸው አያጠራጥርም።
ጄኔራል ባጫ በሺህዎች ወጣት ወታደሮችን እየመራ፣ አምባላጀ ተራራን፣ ግራካህሱ ተራራን በመድፍ እያንቀጠቀጠ – ወዲ ወረደን ሲያራውጥ፣ ምግበ ሃይለን ሲያንቆራጥጥ፣ ወዲ አሸብርን ሲያሸብር፣ ጌታቸው አሰፋን ሲያስደነብር ታይቶኝ “ጊዜ ሸርሙጣ” አልኩ በልቤ። በ’ውነቱ ጄኔራል ባጫ ከዚህ በሁዋላ ቢሞትም አይቆጨው። የጠለሸ ስሙን አድሶአል።
እንዲያው ለነገሩ የጄኔራል ባጫን የዘመናችን የጀግንነት ገድል ሲሰማ ሳሞራ የኑስ ምን ብሎ ይሆን?
close

Leave a Reply