አሮባና ሬስቶራንት

“ኮሮና” ወይም በቅጽል ስሙ “ኮሪ ጭሱ” የተባለው በሽታ ከመምጣቱ በፊት ከእለታት አንድ ቀን ለመዝናናት ወደ አሮባና ሬስቶራንት ሄድኩ።

ብቻዬን ነበርኩ።

ሰዎች እንዳያውቁኝ የጀርመን ጥቁር መነጽር፣ የአሜሪካ ጥቁር ኮፍያ፣ የቬትናም ጥቁር ጫማ እና የእስራኤል ጥቁር ቡታንቲ ለብሻለሁ። ኮርነር ላይ ቦታ ይዤ እየተዝናናሁ ሳለ ማመን የማይቻል አጋጣሚ ከአይኖቼ ተጋጨ።

የዶክተር አብይ አህመድ ባለቤት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ያንን ዝነኛ ፈገግታዋን እንደ ጠላት ገንዘብ ብትን – ብትንትን እያደረገች ወደ ግቢው ገባች።

አስካሉ መንቆርዮስ አጠገቧ አለች።

አስካሉ በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሆስቴስ ነበረች። በዚያን ዘመን አስካሉ ፈገግታዋን (እንደ ጠላት ገንዘብ) ለአይሮፕላን መንገደኞች ብትን – ብትንትን ማድረግ የስራ ግዴታዋ ነበር። ፈገግታዋን ብዙም ሳትበትን ሁሉን እርግፍ አድርጋ ትታ፣ ከአውሮፓ ሆቴል በቀጥታ ወደ ኤርትራ በረሃ ገባች። እና ታጋይ ሆነች። የወጣትነት ፈገግታዋን አራርብ ላይ ቆፍራ ቀብራ ስታበቃም፣ የመትረየስ ጥይት በጠላት ላይ ብትን – ብትንትን ማድረግ ለመደች።

ዞረም ቀረ በአስካሉ እና በዝናሽ ዙሪያ ሌሎች የማላውቃቸው ሰዎችም አብረዋቸው አሉ። የታጠቁ ወይም ያልታጠቁ ስውር የኤርትራ የጸጥታ ሰዎች መኖር አለመኖራቸውን ብፈትሽም ምንም አልነበረም።

በአጋጣሚ አስካሉ እና ዝናሸ ከኔ በቅርብ ርቀት ላይ ነበሩ። የሚነጋገሩትን ሙሉ በሙሉ መስማት ባልችልም በስሜት ተውጠው ድምጻቸውን ከፍ ሲያደርጉ አንዳንድ ቃላት መስማቴ ግን አልቀረም።

close

Leave a Reply