የመቐለ ጦርነት!

ቀዳሚ ግንባር ላይ ያለው አዛዥ ከበላይ አለቃው ጋር በወታደራዊ የመገናኛ ራድዮ ተገናኝቶ እንዲህ አለው፣ “ጠላት እየገሰገሰ በመምጣት ላይ ነው። ካለንበት ምሽግ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ደርሶአል!” አለቃ መልስ ሰጠ፣ “አውቀናል! ችግር የለውም። በአጭር ጊዜ ውስጥ ከባድ ማእበል እንፈጥራለን። አታስብ። አንተ ብቻ ጠንክረህ ተዋጋ!!” ከሁለት ሰአታት በሁዋላ መልሶ የሬድዮ ግንኙነት አደረገ፣ “ጠላት ፈጥኖ እየመጣብን ነው። 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ደርሶአል!” አለቃ መልስ ሰጠ፣ “አውቀናል! አውቀናል!! አይዞህ! ችግር የለውም። ጠንክረህ ተዋጋ ብዬህ ነበርኮ። ታይቶም ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ ህዝባችን ድምጥማጣቸውን ያጠፋቸዋል። አይዞህ! ተረጋጋ!” ከአንድ ሰአት በሁዋላ እንደገና ወደ አለቃው የሬድዮ ግንኙነት አድርጎ ሲያበቃ፣ እንዲህ አለው፥ “ጠላት ምሽጋችን ውስጥ ገብቶአል። ቆይ አንዴ ጠብቀኝ። አጠገቤ አለ። ሊያናግርህ ይፈልጋል!”

close