የፍጻሜው ጦርነት!

አድዋ – ሽሬ – አክሱም በምህጻረ ቃል “አሽአ” ተብለው ሲጠሩ ኖረዋል። “የአብዛኞቹ የህወሓት መሪዎች የትውልድ መንደሮች” ተብለው ይታወቃሉ። (መለስ-ስብሃት-አባይ ወዘተርፈ።) በህወሓት የስልጣን ክፍፍል ውስጥ ልዩ ተጠቃሚ እየተባሉ ሲታሙም ኖረዋል። በዚህ ጦርነት የተረዳነው ግን ተገላቢጦሽ ሆነ። የዚህ አካባቢ ህዝብ ልብ ከወያኔ መሪዎች ጋር አልነበረም።
ትናንት ጌታቸው ረዳ፣ ደብረጽዮን እና ገብረ ገብረጻድቅ በTV ሲናገሩ ሰማሁ። ጌታቸው ቴክሱ መርቅኖ እና ሰክሮ ነበር። አዝናንቶኛል። ደብረጺ በግልባጩ ሶስት ቀናት እህል የቀመሰ አይመስልም። አሳዝኖኛል። ገብረ በአንድ የጦርነት ፊልም ላይ የዋና ተዋናይነት ሚና የተሰጠው ይመስል ደስተኛ መስሎ ታየ። አስገርሞኛል።
ሶስቱ የህወሓት ሰዎች የተመሳሰሉበት ነገር ቢኖር ራሳቸው የሚናገሩትን መልሰው እያፈረሱ በመዘባረቃቸው ነው።
ከሚፈለጉት የወያኔ ሰዎች መካከል ከነፍስ ግድያ ጋር ያልተነካኩ አመራሮች ቢማረኩ ያዋጣቸዋል። ምክንያቱም መሳሳታቸውን ተረድተው፣ ቅጣታቸውን ጨርሰው ለቀሪው ትውልድ የሚጠቅም መጽሃፍ መጻፍ ይችላሉ – እንደ ደርግ ባለስልጣናት።
የሞት ፍርድ የሚጠብቃቸው ግን ከመማረክ እየተዋጉ መሞት ያዋጣቸው ይሆናል። ምክንያቱም በመማረክ እና በመሞት መካከል ምንም ልዩነት አይኖረውም። እዚህ ላይ የሚያስተክዝ ጉዳይ አለ። ከመሞት በቀር አማራጭ የሌላቸው እነዚህ ሰዎች የስንት ንጹሃን ዜጎችን ህይወት ይዘው ይሄዱ ይሆን?
close

Leave a Reply