2021! ተስፋ ወይስ ጨለማ?

ለብርሃነ ልደቱ!
እንዲሁም ለአዲሱ አመት!
በኮረና ቫይረስ አጨናንቆ!
በጦርነት አሳቅቆ!

ፈጣሪ አምላካችን!

መቸም እንደነገሩ አድርሶናል!!
በአምላክ ድርጊት እና ስራ ባልደሰትም. . .
አማራጭ ስለሌለኝ
“እንኩዋን አደረሰን!” እላለሁ!
አምላክ ሰጠ!
አምላክ ነሳ!
እሱ የተመሰገነ ይሁን!!
አምላክ አይወቀስ – ሰማይ አይታረስ!

(በርግጥ አምላክ አማርኛ ከቻለ ይህን ያነበው ይሆናል!)

ዞረም ቀረ!. . .

ወያኔ የተባለው ትልቁ ነቀርሳ ተወግዶአል። ምን ቀረ? በአካባቢ ደረጃ እናስብ ከተባለ ኢትዮጵያውያን ረጋ ብለው ማሰብ ይጠበቅባቸዋል። በተለይ ቀልድ መቀነስ ይገባል። የአሸናፊነት ዘፈን እና ዳንስም አያዋጣም። ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያውያንን አሸንፎ አያውቅም። ቀጣዩ መንገድ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን በሰላማዊ መንገድ ለማስፈጸም መሞከር ብቻ ይመስለኛል።

በ’ውነቱ “የሱዳን ግርግር” አላሳሰበኝም። የግብጽ እጅ ቢኖርበትም እንኩዋ ጉዳዩ የትም አይደርስም። ለአካባቢው ሰላም ሲባል ኢትዮጵያ መታገስ አለባት።

አንዳንደ አክቲቪስቶች፣ “ኢትዮጵያ በአንድ ክፍለጦር – በሶስት ቀናት ካርቱም መግባት ትችላለች!” ሲሉ ጽፈዋል። ሊሆን ይችላል። ይህን መናገር ግን ለምን አስፈለገ? የESAT ጋዜጠኛው ፋሲል በበኩሉ “የአማራ ሚሊሻ ሱዳንን በአለንጋ እየገረፈ” የሚል ባለጌ ተራ የቅስቀሳ አነጋገር መጠቀሙን ሰምቻለሁ። መቸም የአማራ ሚሊሻ ብቻውን ወያኔን እንደደመሰሰ ለማስመሰል የሚሰራጭ ፕሮፓጋንዳ ውሸት ብቻ ሳይሆን አያዋጣም። በመሰረቱ ወያኔን በመደምሰስ ሂደት የአንበሳው ድርሻ የማን ነበር? የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ወይስ የአማራ ሚሊሻ? ታሪክ ወደፊት ይፋ ያደርገዋል። ገና ውጊያው ሳያበቃ ወደ ታሪክ ሽሚያ ወይም ማወዳደር መግባት ግን ለኢትዮጵያ አይጠቅማትም። ባንጻሩ ይጎዳታል!!

ዞረም ቀረ የኔ አስተያየት “በዚህ የሱዳን ጥቃት የግብጽ እጅ እንዳለበት በመረዳት መታገስ ይገባል!!” የሚል ነው።

በውነቱ በመጪው ዘመን በኢትዮጵያ የርስበርስ ግጭት አይቀጥልም። በፍጹም አይቀጥልም። የሚፈራው የርስበርስ ግጭት ከወያኔ ጋር አብሮ ተቀብሮአል። ሰሞኑን በቤኒሻንጉል የታየው አሳፋሪ ግድያ የመጨረሻው የግብጽ መፍጨርጨር ይመስለኛል።

የኦሮሞ ህዝብ የወያኔ ወይም የግብጽ ፍላጎት ደጋፊ ወይም አስፈጻሚ ሊሆን እንደማይችል ግልጽ ነው። የኦሮሞ ህዝብ ሁሉ በእጁ ነው። ሁሉ በደጁ ነው። ጥያቄውን ለማስፈጸም ግብጽ አታስፈልገውም።

የወልቃይት እና የራያ ጉዳይ በምን መልኩ እንደሚፈታ ግልጽ ሆኖአል። “አገሩ የነዋሪዎቹ ነው” ተብሎአል። አበቃ።

የወያኔን ህገመንግስት የማሻሻል ጉዳይ አሁን አንገብጋቢ አይመስለኝም። ከጥቂት አመታት በሁዋላ የአገሪቱ ተመራጮች ሊያስቡበት ይችላሉ።

ባንዴራው ላይ የተለጠፈው አምባሻ አሳሳቢ አይደለም። ህዝቡ ካልፈለገው ሊወገድ ይችላል። የOLF ባንዴራ የኢትዮጵያ ባንዴራ ሊሆንም ይችላል። ጉዳዩን ለሰፊው ህዝብ መተው ይሻላል።

የአልሸባብ ጉዳይ ወዴት እንደሚያመራ የምናየው ይሆናል። የሶማሊያ መረጋጋት ለአፍሪቃ ቀንድ ግድ ነው።

እንግዲህ ምን ቀረ?

አብይ አህመድ ኢትዮጵያን አረጋግቶ፣ በማወቅ የታሰሩትን ቀጥቶ፣ ባለማወቅ የታሰሩትን ፈትቶ ለአፍሪቃ ቀንድ የሚተርፍ ሰላም ያሰፍን ዘንድ እመኛለሁ!!

close

Leave a Reply